እንኳን ወደ አዲስ አበባ ደንብ ማስከበር የቅሬታ መሙያ ሲስተም በድህና መጡ!!

ስለ አቤቱታ አቀራረብና ውሳኔ አሰጣጥ

ሰላም ጤና ይስጥልኝ! ይህ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የባለጉዳይ የቅሬታ ማቅረቢያ ፎርም ሲሆን ባለጉዳይ/ተገልጋይ/ በተገለገለው አገልግሎት ካልተደሰተ/ቅሬታ ከተሰማው ይህንን ቅፅ በጥንቃቄ በመሙላት ለሚመለከተው ክፍል ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል። አገልግሎታችንን ስለተጠቀሙ እናመሰግናለን።

  • ማንኛውም የደንብ መተላለፍ ፈጽሞ የቅጣት ክፍያ የተጣለበት፣ ንብረቱ የተወረሰበት፣ የታሸገበት ሰው ቅጣቱን ከከፈለበት ቀን አንስቶ በሶስት የሥራ ቀናት ውስጥ ጥፋቱ በተፈጸመበት ወረዳ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት መቀጮውን የከፈለበትን ደረሰኝ በመያዝ አቤቱታውን በፅሑፍ ሊያቀርብ ይችላል፣
  • አቤቱታ የቀረበለት የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ላፊ የቀረበለትን አቤቱታ አግባብነትካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብና በመመርመር በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ ለአቤቱታ አቅራቢው በፁሁፍ ምላሽ ይሰጣል፣
  • በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (1) በተሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ቅሬታ አቀራቢ ውሳኔው በተሰጠው በአሥር ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አቤቱታውን ለክፍለ ከተማዉ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት በፅሁፍ ሊያቀርብ ይችላል፣
  • አቤቱታ የቀረበለት የክፍለ ከተማዉ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ሀላፊ የቀረበለትን አቤቱታ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብና በመመርመር በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ለአቤቱታ አቅራቢው በጽሑፍ ምላሽ ይሰጣል፤ በተሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ቅሬታዉን በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ለማዕከሉ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ሀላፊ ማቅረብ ይችላል፣
  • አቤቱታ የቀረበለት የከተማው ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ላፊ የቀረበለትን አቤቱታ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብና በመመርመር በአስራ አምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ለአቤቱታ አቅራቢው በጽሑፍ ምላሽ ይሰጣል፣
  • በዚህ አንቀፅ በተሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ቅሬታ አቀራቢ ወደ ሚመለከተው የፍትህ አካል ቀርቦ አቤቱታውን ማሰማት ይችላል፣
  • በዚህ አንቀፅ በአንደኛው አካል አቤቱታው ተመርምሮ ትክክለኛነቱ ሲረጋገጥ አላግባብ የተከፈለው ቅጣትና የተወረሰው ንብረት ይመለሳል፣ ወይም የታሸገው ቤት ይከፈታል፤ የተከፈለው የቅጣት ገንዘብ በከተማው አስተዳደር ፋይናንስ ስርዓት መሰረት ለአቤቱታ አቅራቢው ተመላሽ እንዲደረግ ቅጣቱ አላግባብ ነው በማለት ውሳኔውን የሰጠው አካል ገንዘቡ ገቢ ከተደረገለት ከወረዳው ፋይናንስ ወጭ ተደርጎ እንዲሰጥ በፁሁፍ ያሳውቃል፣
  • በዚህ አንቀፅ የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ አቤቱታ አቅራቢው የተወረሰው ንብረት ይመለስልኝ የሚል አቤቱታ ከማቅረቡ በፊት እና ቅሬታው ትክክል ነው ብሎ ከወሰነው አካል ውሳኔ በፊት ንብረቱ ተሽጦ ገቢ እንደሆነ ሊመለስለት የሚችለው የከፈለው የቅጣት ገንዘብና ንብረቱ ተሸጦ ገቢ የሆነው ገንዘብ ነው፡፡
  • አድራሻ

    አዲስ አበባ ደንብ ማስከብር ማስደበር አድራሻ

    አድራሻ

    ፒያሳ በተለምዶ እሪ በከንቱ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ EMA ታወር ከ7ኛ-13ኛ ወለል

    ስልክ ቁጥር

    0115621721 or 9995

    ኢሜል

    Codeenforcement05@gmail.com